የኮቪድ - 19 ወረርሽኝን ለመከላከል መሚደረገው ጥረት የኢሴሃማ ድርሻ

Updated: May 19, 2020

ዛሬ አለማችንን ከመቼውም ጊዜ በላይ በኮቪድ - 19 (ኮሮና ቫይረስ በሽታ 2019) ተብሎ በሚጠራው ወረርሺኝ ምክንያት በፈታኝ ሁኔታ ውስጥ ትገኛለች።  ሃገራትም ይህንን ወረርሽኝ ቢችሉ ለመከላከል ካልሆነም ስርጭቱንና ለመግታትና የሚያስክትለውን ቀውስ ለመቀነስ የተለያዩ ጥረቶችን እያደርጉ ይገኛሉ። ሃገራችንም ወረርሽኙ በቻይና እንደተከሰተ ከታወቀበት ከጥር ወር ጀምሮ ቫይረሱ ህመም ያስከተለባቸው ሰዎች እስከተገኙበት መጋቢት 4 2012 እና ከዚያም ወዲህ የተለያዩ እርምጃዎች እየተወሰደ ያለ ሲሆን፤ የጤና ባለሙያዎች ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በመሆን ይህንን ወረርሽኝ የመከላከል ትልቅ ሃገራዊ ሃላፊነት የተጣለባቸው እንደሆነ ይታወቃል።  በመሆኑም የኢሴሃማ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በዚህ ወቅታዊ መግለጫ አውጥትዋል። በተጨማሪም የግንዛቤ ማስጨበጫ መረጃዎችን በማህበራዊ ድህረ ገፁ ላይ ማስተላለፍ ጀምርዋል።